2.9.13. የሰው ሀብት አስተዳደር ክፍል 


2.9.13.1. የሰንበት ት/ቤቱን የሰው ሀብት አደረጃጀት የተመለከተውን ሥራ በዕቅድ መምራት፤
2.9.13.2. የሰንበት ት/ቤቱን የአባላት ቅበላ፣ ምደባ እና ቅቡል ሥራዎችን ማከናወን እና መምራት፤
2.9.13.3. የአባላትን ቅቡል መሠረት ያደረገ የሰው ኃይል ድልድል ማዘጋጀት፤
2.9.13.4. የሰንበት ትምህርት ቤቱን ደጋፊ አባላት ለተለያዩ ሥራዎች ማስተባበር፤
2.9.13.5. የአባላት መንፈሳዊ ሕይወት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መከታተል ፤ ባልታወቀ ምክንያት ሲርቁ እንዴት እና በምን ምክንያት እንደራቁ በማጥናት ለሥራ አስፈጻሚው ጉባኤ እና ለሥራ አመራሩ ማሳወቅ፣ የመፍትሔ አቅጣጫ ማመላከት፤
2.9.13.6. ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉም ሆነ በክፍለ ሀገር ያሉ አባላትን መንፈሳዊ ሕይወት እየተከታተሉ የሚጠበቅባቸውን መንፈሳዊ ግዴታ እንዲያሟሉ ከሰንበት ት/ቤቱ ሊደረግላቸው የሚገባውን ሁሉ ከመመሪያና ደንቡ በሚስማማ ሁኔታ ማስፈጸም፤
2.9.13.7. በሰንበት ት/ቤቱ የሥራ አመራር ጉባኤ የሚወጡ አዳዲስ መመሪያዎችን በተለያየ መልኩ በአባላት እንዲተገበሩ ማድረግ፤
2.9.13.8. በሰንበት ት/ቤቱ በሚዘረጉ የመርሐ ግብር ማዕቀፎች ላይ የስም ቁጥጥር ማድረግ፤
2.9.13.9. በተደጋጋሚ የሚቀሩ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና የረፈዱትን እየተከታተሉ የስም ዝርዝራቸውን በማውጣትና ሌሎችንም አማራጮች በመጠቀም መፍትሔ መስጠት፤
2.9.13.10. በአባላት ላይ ለሚከሰቱ የህዘን እና የደስታ መርሐ ግብሮች እና ለመሰሉት አገልግሎቶች አስፈላጊውን መረጃ ለሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በመስጠት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፤
2.9.13.11. ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እንደ ሥራው ዝርዝርና ኃላፊነት ይከታተላል፤
2.9.13.12. በአባላት ምልመላ፣ ቅቡል እና ሥምሪት አስተዳደር ሥርዓት መሠረት ያደረጉ ሥራዎች እንዲከናወኑ አቅጣጫዎችን ማውጣት፤ እንዲሁም የሰንበት ት/ቤቱ አባላት ተቋማዊ አደረጃጀቶች ላይ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፤
2.9.13.13. የአባላት መረጃ፣ ድጋፍና ክትትል ሥራን በዘላቂነት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ዘላቂ ዓላማ አኳያ በዕቅድ አዘጋጅቶ መተግበር፤
2.9.13.14. አባላት የሰንበት ት/ቤቱ ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው መሥራትና ማስተባበር የሚችሉበት የአመራር ማሳደጊያ ሥርዓት በመተግበር የማበረታቻ እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት ይተገበራል፤
2.9.13.15. ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የክፍሉን አገልግሎት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጸድቀው ስልታዊ ዕቅድ፣ መመሪያና አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡