About Us
Who We Are & What We Believe
የውሉደ ብርሀን ሰንበት ትምህርትቤት ታሪክ
የደብሩ መመሠረት መንፈሳዊ ብርሃኑን ሲያበራ፣ አብሮ የተወለደው የውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ደግሞ የሕፃናትና የወጣቶች መጠጊያ ሆነ። በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም በስድስት አባላት አነስተኛ ቁጥር የተጀመረው ይህ ማኅበር፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አማካኝነት “ውሉደ ብርሃን” (የብርሃን ልጆች) የሚል ታላቅ ስም ተሰጠው። በወቅቱ ወጣቶቹ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ውስጥ እንደ ሕንፃ ሰናዖር ያሉ ድራማዎችን በቲያትር መልክ እያቀረቡ እምነታቸውን ያደምቁ ነበር።
ነገር ግን መንገዱ አልጋ በአልጋ አልነበረም። በ1960ዎቹና 70ዎቹ መጨረሻ በሀገሪቱ ላይ የሰፈነው የደርግ አብዮትና የሶሻሊዝም ርዕዮተ-ዓለም ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ትልቅ ፈተና አ አመጣ። ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይመጡ በቀበሌ «ኪነት» እና በአብዮታዊ መዝሙራት ተጠመዱ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚቀርቡትም «ኋላቀር» ወይም «አይዲያሊስት» እየተባሉ ይገፉ ነበር። ነገር ግን በጥቂት ጽኑ ወጣቶችና መምህራን ጥረት ማኅበሩ ሳይበተን ማህሌቱንና አገልግሎቱን በጽናት አስቀጠለ።
በ፲፱፻፸ዎቹ መጨረሻ ደግሞ ሌላ የለውጥ ምዕራፍ ተከፈተ። በቤተ ክርስቲያኗ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኩል ለታዳጊዎች ደብተር፣ መጽሐፍና አልባሳት ይከፋፈል ስለነበር፣ ወደ 400 የሚጠጉ ሕፃናት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ፈሰሱ። የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልጋዮች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሕፃናቱን በቡድን ከፍለው ሃይማኖትን፣ ታሪክንና አምስቱ አዕማደ ምስጢርን ያስተምሯቸው ጀመር። በዚያ ፈታኝ ዘመን በእምነት የታነጹት እነዚያ ሕፃናት፣ ዛሬ አድገው የሰንበት ትምህርት ቤቱና የደብሩ ዋና አባቶችና መሪዎች ለመሆን በቁ።
ዛሬ ላይ ያለው ውሉደ ብርሃን
ትናንት በችግኝ ደረጃ የተተከለው ውሉደ ብርሃን፣ ዛሬ ታላቅ ዋርካ ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት ከሕፃናት እስከ 9ኛ ክፍል ያሉ 11 የትምህርት ክፍሎችን ዘርግቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችን የሚያስተምር፣ በየዓመቱ ዲያቆናትን የሚያፈራ የትምህርት ማዕከል ነው።
የራሱን ባለ G+2 ሕንፃ ገነብቶ የመማሪያ አዳራሾችን፣ ቤተ-መጽሐፍትን፣ የልማትና የካህናት ንስሐ ልጆች ማስተማሪያ ክፍሎችን በማዘጋጀት የትውልድ ኮትኳችነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ታሪክ
የደብሩ ታሪክ የሚጀምረው ከእንጦጦ ተራራ አየር በላይ መንፈሳዊ ተስፋ በተሰነቀበት በዚያ ቀደምት ዘመን ነው። የታቦተ ሕጉ አመጣጥ ታሪክ ከሩቅ ከእነሞር (ከአጫዋዳ ሥላሴ) የሚመዘዝ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ የመጀመሪያ ማረፊያው ያደረገው የመንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ነበር።
ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ በፊት ታቦቱ በጽናት በእንጦጦ ምድር እንዲተከል ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ የሀገሪቱ በወረራ ማዕበል መመታት ሥራውን ለጊዜው አስተጎደለው። ጠላት ሀገሪቱን በወረረበት ወቅትም የደብሩ መሥራች የሆኑት የጽናት አባት አባ ኃይለ ሥላሴ የሚኖሩበት ቦታ በጠላት ተወስዶ፣ በቦታው ላይ የነበረው ድንጋይ በድማሚት እየተናደ ለጠላት መንገድና ሕንፃ መሠሪያ ይሆን ነበር።
ነገር ግን የወረራው ጨለማ ገፎ ሀገር ነፃ ስትወጣ፣ የአባ ኃይለ ሥላሴ ሕልም እንደገና አሰፈሰፈ። በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም አባ ኃይለ ሥላሴ ለመኖሪያቸው በተሰጣቸው ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያኑን ለመትከል ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መልእክት ላኩ። ንጉሠ ነገሥቱም፦ “ይህ የምትኖርበት ቦታ ወደ ውስጥ የገባ ስለሆነ አንተ ኑርበት፤ ቤተ ክርስቲያኑ ግን ለሰውም ለመንገድም ቅርብ በሆነው ስፍራ ወደ መንገድ ወጣ ብሎ ይሥራ” በማለት የመረጡትን ቦታ አመለከቱ።
በዚሁ መሠረት በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም ሐምሌ ፯ ቀን ቦታው በእጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) ተባርኮ የመሠረቱ ድንጋይ ተጣለ። በቀጣዩ ዓመት ህዳር ፮ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ፣ እቴጌ መነንና የመንግሥቱ ባለሥልጣናት በተገኙበት የመዓዘኑ ድንጋይ በክብር ተቀመጠ። አባ ኃይለ ሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ መሠራት የነበራቸውን መሬትና የከተማ ቤታቸውን እስከ መሸጥ፣ ቦታቸውን አሲዘው ባንክ ብድር እስከ መውሰድ ድረስ ታላቅ መንፈሳዊ መሥዋዕትነት ከፈሉ።
በታላቅ ርብርብ የተሠራው ሕንፃ ተጠናቆ ግንቦት ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ከመቃኞ ወጥቶ ወደ አዲሱ ሕንፃ ሲገባ በኢትዮጵያ ሬድዮ ታላቅ ዜና ሆኖ ተበሰረ። ለደብሩ አገልግሎትም 15 የመጀመሪያ ካህናት ከየአድባራቱ ተመርጠው መሬት ተሰጥቷቸው በቦታው ተተከሉ።
ጊዜያት አልፈው ያ አሮጌ ሕንፃ ባረጀ ጊዜ፣ ምዕመናን፣ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ቀን ከሌሊት በልመናና በበጎ አድራጎት ገንዘብ በማሰባሰብ ታላቁን አዲስ ሕንፃ ገነቡ። ህዳር ፯ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ አዲሱ ሕንፃ ተመርቆ ታቦቱ ሲገባ፣ የእድሜ ባለጸጋ የሆኑ አባቶችና እናቶች በደስታ እንባ ይላቀሱ ነበር።