2.9.17. የልማትና በጎ አድራጎት ክፍል
2.9.17.1. የሰንበት ት/ቤቱን የበጎ አድራጎት እና ልማት ሥራዎች ከማዕከል በሚወጣው መመሪያ በዕቅድ ይመራል፤
2.9.17.2. አባላት በተለያየ መልኩ በኢኮኖሚ እና መሰል የኑሮ ችግር ሲደርስባቸው በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት ችግሩን በማጥናት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
2.9.17.3. በአጥቢያው አካባቢ ያሉ ነዳያን ልጆቻቸውን እና ራሳቸውን የሚችሉበትን ፕሮጀክት እያጠና የሚደገፉበትን መንገድ ያመቻቻል፤
2.9.17.4. ነዳያን እንደ ዕድሜያቸውና ልማት መንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚጎለብትበትን መርሐ-ግብር በማዘጋጀት ትምህርት እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር መርሐ ግብር ያዘጋጃል፤
2.9.17.5. በኑሮ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘት በነርሲንግ ሥራ የተፈጠረ ሰው ከመሆን እንደማያንስ የሚያስገነዝቡ የሃይማኖት፣ የሥነ ምግባርና የሥነ ልቦና ትምህርት በጉባኤያቸው ላይ እንዲሰጥ ማድረግ ፤፤ ጉባኤውንም በቅርብ መከታተል እና ይመራል፤
2.9.17.6. ነዳያንን እንደ የዕድሜያቸው እና እንደየፍላጎታቸው በትምህርተ ሃይማኖት፣ በስብከተ ወንጌል፣ በመንፈሳዊ መዝሙር ፣ በሥነ ጽሑፍ እና በመንፈሳዊ ጨዋታዎች እንዲሁም በመሰሉት ሁሉ ስብስብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማበረታታት እና ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
2.9.17.7. ችግረኛ ወጣቶችን የተለያዩ ሙያዎችን በመቅሰም እና ሥራ በመሥራት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የአጭር ፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የሙያ ሥልጠናዎችና የተለያዩ የሥራ ዕድሎች እንዲያገኙ ከሚመለከተው ክፍል ጋር ያመቻቻል፤
2.9.17.8. በዕለተ ሰንበት ቤተክርስቲያን ዙሪያ የወደቁትን እና በብቸኝነት ሁኔታ ተጠልለው የሚገኙ የመጠለያ ቤት ችግር ያለባቸው ነዳያን የመጠለያ ቤት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ያመቻቻል፤
2.9.17.9. የጤንነት ችግር ያለባቸውን ተረጂዎች የጤና ሁኔታቸውን ለማሻሻል ይቻል ዘንድ ከጤና ጣቢያዎች ከክሊኒኮች እና ከሆስፒታሎች ነፃ ሕክምና ወይም በዝቅተኛ ዋጋ ሕክምና የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
2.9.17.10. ችግረኞች እርስ በርሳቸው መረዳዳትና መተሳሰብ እንዲችሉ፤ ፍቅር እንዲኖራቸው በማድረግ ራሳቸው ተቋቁመው በማኅበራት ተደራጅተው ሌሎችን ሊረዱ የሚችሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
2.9.17.11. አባላት በተለያየ ምክንያት ጤንነታቸው ሲታወክ፣ ሐዘን ሲደርስባቸው እና ወዘተ ድጋፍ በሚያስፈልግበት ወቅት በቤት፣ በሆስፒታል በሕክምና ቦታ በመገኘት የሚረዱበትን መንገድ ያመቻቻል፤
2.9.17.12. በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚገኙ አብነቶች ያረጁ የጤና ልዩ ልዩ ችግር ያለባቸውን ገዳማት እና አድባራት በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር እርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
2.9.17.13. አባላት ያላቸውን ሙያ (በተግባረ ዕድ፣ በልብስ ስፌት፣ በጥልፍና፣ በእንጨት ሥራ፣ በብረታ ብረት፣ በግንባታ ሙያ ወዘተ) በማስተባበር አስፈላጊውን የቁሳቁስ አቅርቦት በማዘጋጀት ለሽያጭ የሚውልበትን መንገድ ያመቻቻል፤
2.9.17.14. በተለያዩ በዓላት ላይ ልዩ ልዩ የኅትመት ፤ የምስልና ድምፅ ሌሎችንም መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን ዕቃዎች በማቅረብ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር የገቢ ሥራ ያከናውናል፤
2.9.17.15. የሰንበት ትምህርት ቤቱ የልማት ሥራ እና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት የኢኮኖሚ ልማት ሥራዎችን ከማዕከል በሚወጣው መመሪያ እና እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በፕሮጀክቶች በመቅረጽ እያስጸደቀ ተግባራዊ ያደርጋል፤
2.9.17.16. በሰንበት ት/ቤቱ መዋቅሮች የሚካሄዱ የልማትና የገቢ ማግኛ እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ይከታተላል፤
2.9.17.17. ችግረኛ ወጣቶችን የተለያዩ ሙያዎችን በመቅሰም እና ሥራ በመሥራት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የአጭር ፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የሙያ ሥልጠናዎችና የተለያዩ የሥራ ዕድሎች እንዲያገኙ ከሚመለከተው ክፍል ጋር ያመቻቻል፤
2.9.17.18. በሰንበት ት/ቤቱ የሥራ አመራር ጉባኤ በኩል ከደብሩ የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር በበሽታም ሆነ በዕድሜና እርዳታ ተደርጎላቸው ሊሽሉአቸው ያልቻሉ እና ያረጁ ነዳያንን ነጻ ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸው በአግባቡ የተቀበሩበት ሥነሥርዓት የሚፈጸምበትን መንገድ በቋሚነት ያሰናዳል ፤
2.9.17.19. በመዋጮም ሆነ በስጦታ ለችግረኞች ተብሎ በእርዳታ የተገኘ ገንዘብና ንብረት ወይም ቁሳቁስ ለሚመለከታቸው ችግረኞች በትክክል መድረሱንና በአግባቡ መታደሉን መቆጣጠር፤ አፈጻጸሙንም ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያደርጋል፤
2.9.17.20. የተሰበሰበውንም ሆነ የተከፋፈለ የእርዳታ ገንዘብና ንብረት መጠንና ዓይነቱን በትክክል መመዝገብ እንዲያዝ እና ለሚመለከተው ክፍል እንዲቀመጥ ያደርጋል፤
2.9.17.21. በሰንበት ት/ቤቱ ካሉ የአገልግሎት ክፍሎች ጋር በመተባበር የተለያዩ ሥራዎችን በማዘጋጀት የሽያጭ (ገቢማግኛ) ተግባር ያከናውናል፤
2.9.17.22. በቤተክርስቲያናችን ዓመቱን ሙሉ የሚከበሩ ልዩ ልዩ በዓላትን መሠረት በማድረግ መሊያይዩ ቦታዎች መንፈሳዊ የጉዞ መርሐ-ግብር በማዘጋጀት ምዕመናንን ከነጋዲው በረከት ተካፋይ በማድረግ ብሎም ለሰንበት ት/ቤቱ የገቢ ምንጭ ይፈጥራል፤
2.9.17.23. በሰንበት ት/ቤቱ የሚገኙ የተለያዩ ቁሳቁሶች (የእንጨት ሥራ ውጤቶችን ፣ የኤሌክትሪክ ፣ የፅሕፈት ወዘተ) ብልሽት ሲያጋጥማቸው በመጠገን (በማስተካከል) አገልግሎት ላይ የሚውሉበትን መንገድ ያመቻቻል፤
2.9.17.24. ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የክፍሉን አገልግሎት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጸድቀው ስልታዊ ዕቅድ፣ መመሪያና አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡
2.9.17. የልማትና በጎ አድራጎት ክፍል
Announcement August 12, 2026
Announcement
33 views
Back to Announcements