2.9.14. የመረጃ እና የውስጥ ግንኙነት ክፍል
ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ሆኖ
2.9.14.1. የሰንበት ት/ቤቱ መረጃ እና የውስጥ ግንኙነቶች አሠራር በዕቅድ እንዲተገበር ያደርጋል፤
2.9.14.2. የሰንበት ት/ቤቱን የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት መምራት፣ ማስተባበር እና በክፍሎች መካከል ያሉትን የአፈጻጸም ተመሣሣይነት ያሰንብታል፤
2.9.14.3. በቋሚነት ሰንበት ት/ቤቱን መረጃ ማሰባሰብ፣ ማደራጀት በሥራ አመራሩ ሲፈቀድ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፤
2.9.14.4. የአባላትን ግላዊ መረጃ (Biography) በመሰብሰብ በሰነድና በኮምፒውተር የመረጃ መረብ ያደራጃል፤
2.9.14.5. የሰንበት ትምህርት ቤቱን ሰነዶች በተጠና መልኩ ማዘጋጀት እና ይጠብቃል፤
2.9.14.6. የሰንበት ት/ቤቱን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በጽሑፍ ፣ በምስልና በድምፅ ዘገባ ያደራጃል፤
2.9.14.7. የተዘገቡ የድምፅና የምስል ሥራዎች በአግባቡ የቤተክርስቲያናችንን እምነትና ሥርዓት በጠበቀ መልኩ የቅንብር (ኤዲቲንግ) ሥራዎችን ያስተባብራል፤
2.9.14.8. በተለያየ መልኩ የሚሰበስባቸውን መረጃዎች ዓይነትናቸውና በቊጥር ለአገልግሎት በሚያመች መልኩ በቤተ መዛግብት ያከማቻል፤
2.9.14.9. በሰንበት ት/ቤቱ የሚገኙ ክፍሎችን ሥራ የሶፍትዌር ፕሮግራም የጽሕፈት ሥራን ያቀናጃል፤
2.9.14.10. በመደበኛ የክፍሎች ስብሰባ ወቅት እና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች የክፍሎችንና የሥራ አስፈጻሚ አካላትን የሥራ ሂደት ሪፖርት ያጠናቅራል፤
2.9.14.11. በየዘርፉ ያለውን የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ስታትስቲካዊ መረጃ ያዘጋጃል፤
2.9.14.12. የሰንበት ት/ቤቱን ዓመታዊ የአባላት መንፈሳዊ ጉዞን ያዘጋጃል፤
2.9.14.13. ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እንደ ሥራው ዝርዝርና ኃላፊነት ይከታተላል
2.9.14. የመረጃ እና የውስጥ ግንኙነት ክፍል
Announcement August 12, 2026
Announcement
33 views
Back to Announcements