2.9.12. የመርሐ ግብርና ጉባኤያት ክፍል
ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ሆኖ
2.9.12.1. የሰንበት ት/ቤቱን የመርሐ ግብር እና ጉባኤያት ሥራ በተጠና እና በተደራጀ መልኩ በዕቅድ እንዲመራ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲናበብ ያደርጋል።
2.9.12.2. በሰ/ት/ቤቶች ወጥ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የሚማሩ በቅድመ መደበኛ ሕፃናት፣ መደበኛ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል የሕፃናት፣ ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የታዳጊዎች፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የወጣቶች ትምህርት እርከን እና በልዩ መደበኛ አባልነት የሚካተቱ አባላትን ታሳቢ ያደረገ አንድ ሰንበት ት/ቤት የጋራ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ጉባኤትና መርሐ ግብራት ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመናበብ ያስተባብራል።
2.9.12.3. ሃይማኖታዊ እና የሕዝብ በዓላትን በመጠቀም ለሰንበት ት/ቤቱ አባላት ፣ ለአካባቢው ምዕመናን እና ለሌሎች ልዩ ጉባኤያትን ማዘጋጀት ፣ ማስተባበር ፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል ፤
2.9.12.4. ያደራጃቸውን ጉባኤያት ወደ መደበኛነት በመቀየርም ይሁን በጊዜያዊነት በመከታተል ስታትስቲካዊ መረጃ መያዝ፤
2.9.12.5. የሰንበት ት/ቤቱን አጠቃላይ መንፈሳዊ መርሐግብሮች ለምዕመናን የማስተዋወቅ ሥራ ማከናወን ዘመኑ በፈቀደው ቴክኖሎጂ ሁሉ በማኅበራዊ መገናኛ፣ በዌብሳይት፣ በካሴት፣ በኅትመት፣ በእጅ በመጻፍ የመሳሰሉትን መንገዶች በመጠቀም ነባር እና አዲስ አባላትን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ መርሐ ግብር እንዲመጡ ያስተዋውቃል፤
2.9.12.6. በሰንበት ት/ቤቱም ሆነ በክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱትን የጸሎት መርሐ ግብሮች በወቅቱ እና በሰዓቱ እንዲካሄዱ ያደርጋል ፤
2.9.12.7. ክፍሎችን እንደ አስፈላጊነታቸው በማስተባበር በሚኖሩት በማንኛውም ጉባኤያት ላይ መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንዲፈጸሙ ማድረግ ፤ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል ፤
2.9.12.8. በሰንበት ት/ቤቱ ያሉትን ጉባኤያት አካሄድ እየተከታተለ እንዳይቀንሱና ትምህርት አሰጣጡ በትክክል መሰጠቱን የሚከታተል እና የጎደለው እያየ እንዲስተካከል ያስተባብራል ፤
2.9.12.9. እያንዳንዳቸው ባለድርሻ ክፍሎች የሚያቀርቡት የመርሐ ግብር ጥራት እና ደረጃ እንዲሁም ብቃት አንጻር እየመዘነ በሦስት ወሩ የጋራ የመመካከርያ ስብሰባዎችን በመመሥረት የትግበራ ሥራውን ያከናውናል ፤
2.9.12.10. የጉባኤያትን ይዘት ደረጃ ማውጣት፣ ጥራታቸውን ይቆጣጠራል፣ ያስተባብራል ፤
2.9.12.11. ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የክፍሉን አገልግሎት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጸድቀው ስልታዊ ዕቅድ፣ መመሪያና አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡
አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡
2.9.12. የመርሐ ግብርና ጉባኤያት ክፍል
Announcement August 12, 2026
Announcement
36 views
Back to Announcements