2.9.18. የበጀትና ንብረት አስተዳደር ክፍል
2.9.18.1. የሰንበት ት/ቤቱን የበጀት ድልድል ሥርዓት እና የንብረት አስተዳደሩን በዕቅድ ይመራል
2.9.18.2. የሰንበት ት/ቤቱን መደበኛ የገቢ እና ወጪ ሥርዓት መፈጸም ፤ መከታተል እና ይቆጣጠራል ፤
2.9.18.3. አጠቃላይ የበጀት ድልድል ትግበራን ያከናውናል፤
2.9.18.4. የገንዘብ አሰባሰብና አጠቃቀም ቁጥጥርን ዘመናዊ በሆነ መንገድ መቆጣጠር፤ የተደራጁትን መረጃዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲያዙ ያደርጋል፤
2.9.18.5. በበጀት ተለይተው ወደ በጀት ማስተዳደሪያ ቋት የገቡ ሒሳቦችን ማውረድና ክፍያቸው እንዲፈጸም ማድረግ፤
2.9.18.6. ልዩ ልዩ የበጀት እና የንብረት ሪፖርት ሥራ ለአስፈጻሚ ጉባኤው በሚፈልግበት ወቅት አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
2.9.18.7. የሥራ ማስኬጃና ጥቃቅን ወጪዎች (Petty Cash) ክፍያ ይፈጽማል
2.9.18.8. የዕለት ገንዘብ በመሰብሰብ በሰንበት ት/ቤቱ የገንዘብ የሒሳብ ማጠራቀሚያ ውስጥ ማስገባት፤ ሰነዶችን በመሰብሰብ ለሒሳብ ሹም ያስረክባል፤
2.9.18.9. የገንዘብ መጠን (Cash Position) ሪፖርት አዘጋጅቶ በየዕለቱ ማቅረብ፤ ከሒሳብና ንብረት አስተዳደር ማስተባበሪያው ሹም ጋር በቅርብነትና በጥምረት አብሮ ይሠራል
2.9.18.10. ክፍያ ለተፈጸመላቸው አካላት ክፍያው በተፈጸመ በ5 ቀናት ውስጥ ማውራረዳቸውን፤ በተገቢው ሰነድ መደገፋቸውን ማረጋገጥ፤ ተገቢ ሰነድ ላልቀረበና በተቀመጠው ቀን ያላወራረደ እንደሆነ ለውሳኔ ሰጪ አካል ሪፖርት ማድረግ፤
2.9.18.11. የሰንበት ት/ቤቱ አጠቃላይ ንብረቶችን በንብረት ማስተዳደሪያ ደንብ መሠረት እየተጠበቁና ንብረቶቹ ላይ አደጋና ብክነት እንዳይደርስባቸው ያስተዳድራል፤
2.9.18.12. የሰንበት ት/ቤቱን የግዢ ሥራ በኃላፊነት ይከታተላል፤
2.9.18.13. የተበላሹ የወደቁና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ንብረቶችን ይዞታ ለሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ያሳውቃል፤
2.9.18.14. የጽዳት፣ የቢሮ አስተዳደር፣ የንብረት አጠቃቀምና ጥበቃ፣ የንብረት ኦዲትና ተዛማጅ ሥራዎችን በኃላፊነት ይፈጽማል፤
2.9.18.15. ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የክፍሉን አገልግሎት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጸድቀው ስልታዊ ዕቅድ፣ መመሪያና አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡
2.9.18. የበጀትና ንብረት አስተዳደር ክፍል
Announcement August 12, 2026
Announcement
23 views
Back to Announcements