2.9.15. የመዝሙር እና የሥነ ጥበብ ክፍል ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ሆኖ
2.9.15.1. በሰንበት ት/ቤቱ ውስጥ የሚከናወኑ መዝሙራት እና በዓላት አገልግሎቶችን ከማዕከል በሚወጣው መመሪያ መሠረት በዕቅድ ይመራል፤
2.9.15.2. መዝሙር ንዑስ ኮሚቴዎችን ማደራጀት ፣ በክፍሉ ውስጥ ያለውን የመዝሙራት ማኅደር፣ የአባላትን ልብሰ ስብሐት እና የመዝሙር መገልገያ መሣሪያዎችን በአግባቡ ማስተዳደር እና አያያዛቸውን ይከታተላል፤
2.9.15.3. ለአባላቱ አስፈላጊው የመዝሙር ትምህርት እና ሥልጠና እንዲሰጥ ጊዜውን ማመቻቸትና አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
2.9.15.4. በልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ድርሰቶች መዝሙራትን ማደራጀት፤ በሰንበት ት/ቤቱ ውስጥ የሚጠየቁትንም ሆነ ከውጭ በጥያቄ ለሚቀርቡ ጥናቶች አስፈላጊውን የመዝሙር ሥልጠና መስጠት፤
2.9.15.5. የመዝሙር ሀብቶቻችንን በሲዲ፣ በካሴት፣ በVCD ፣ በሌሎች የቴክኖሎጂ አሠራሮች በማዘጋጀት ከመንበረ ፓትርያርክ መዝሙርና በዓላት ዋና ክፍል አስገምግሞ ለኅትመት እንዲበቁ ያደርጋል፤
2.9.15.6. በወረብ ትምህርት እና ሙያዊ ሥልጠና የተደራጀ አገልግሎት መፍጠር እንዲቻል መሥራት ፤ ከሙያው ጋር ያሉ መምህራንን በማማከር የቀረጹ መርሐግብሮችን ያከናውናል፤
2.9.15.7. የተለያዩ ክብረ በዓላትን መሠረት ያደረገ የአንድ ዕለት ወጥ የአገልግሎት ሥርዓትን የተከተለ የአብነት ወንበር ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት እና አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
2.9.15.8. የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላትን ያማከለ የውጭ አገልግሎት በቁጥርና በዕቅድ ማካሄድ፤
2.9.15.9. መንፈሳዊ የዜማ መሣሪያዎች ሥልጠና ለክፍሉ እና ለሰንበት ት/ቤቱ አባላት የሚሰጥበትን መንገድ ማመቻቸት፤
2.9.15.10. አባላት ያላቸው ልዩ ተሰጥኦ ራሱን የቻለ ሙያ እንዲሆናቸው የልዩ ተሰጥኦ ማልማት መርሐግብር ማዘጋጀት፤
2.9.15.11. ከማዕከል በሚዘጋጀው መመሪያ መሠረት የአደባባይ የጋራ እና በአጥቢያው ያሉ ዓመታዊ ክብረ በዓላትን እና የሰንበት ት/ቤቱን በዓላት የተመለከቱ የአካባቢ ቅድመ ዝግጅት ማካሄድ እና በዓላቱን በሚጠበቀው መልኩ እንዲከበሩ ያስተባብራል
2.9.15.12. ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የክፍሉን አገልግሎት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጸድቀው ስልታዊ ዕቅድ፣ መመሪያና አሠራሮች ጋር ተናበው እንዲፈጸሙ ያደርጋል። እንዲሁም ከመመሪያ እና ከደንብ የመነጩ የሥራ ዝርዝሮች እያካተተ ይሠራል፡፡
2.9.16.1. የሰንበት ት/ቤቱን የኪነ ጥበብ እና ሥነ ጥበብ ሥራዎች በዕቅድ ይመራል
2.9.16.2. የሰንበት ት/ቤቱን አባላት በክፍሉ መሠረታዊ የሥራ ባሕርይ አማካኝነት ለአገልግሎት ዝግጁ ያደርጋል፤
2.9.16.3. በሰንበት ት/ቤቱ የሚቀርቡ ሥነ ጥበባዊ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት ፣ መገምገም እና ማሻሻያዎችን ፤ ለተዘጋጁት ጽሑፎች በወቅቱ በቂና የተሟላ አስተያየት እና ውጤት ይሰጣል፤
2.9.16.4. በሰንበት ት/ቤቱ ውስጥ መንፈሳዊ የሆኑ ቲያትር፣ ሥነ ጽሑፍ ፣ ሥነ ሥዕል እና የጥበብ ዕድ ሥራዎችን እንደ አስፈላጊነታቸው ዝግጁ ያደርጋል፤
2.9.16.5. በሥነጥበብ ክፍሉ መሸፈን ያለባቸውን መርሐ ግብሮች በሙሉ ያዘጋጃል፤
2.9.16.6. በሥነጽሑፍ፣ በቅኔና በመድረክ ዝግጅት፣ በሥነ ሥዕል (በፎቶግራፍ እንዲሁም በልዩ ልዩ የዕደ ጥበብ ሥራዎች ለክፍሉ አባላትም ሆነ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት በትምህርት እና ሥልጠና ክፍሉ በኩል ሥልጠና ያዘጋጃል፤
2.9.16.7. በጥበቦች ላይ ብቃት ያለው የሥነ ጽሑፍ ትምህርት የሚሰጥበትን ዘዴ ማዘጋጀት፤
2.9.16.8. ማንኛውንም የሰንበት ት/ቤቱን ሥነ-ጥበባዊ ሥነ-ጽሑፎችን መገምገም፤ በመድረክም ላይ በአግባቡ ተጠንተው መቅረባቸውን ይከታተላል፤
2.9.16.9. ሌሎች ሥራዎች ከመመሪያና ከደንብ የመነጩ ሆነው ሲገኙ የሥራ ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
2.9.15. የመዝሙር እና የሥነ ጥበብ ክፍል
Announcement August 12, 2026
Announcement
48 views
Back to Announcements