2.9.11. ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል

2.9.11.1. የሰንበት ትምህርት ቤቱን የትምህርት ሥርዓት በዕቅድ እና ወጥ በሆነ አፈጻጸም መምራት፤
2.9.11.2. ሰንበት ት/ቤቱ የተተኪ ትውልድ ማፍሪያ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተቋማት እንደመሆኑ መጠን ከመንበረ ፓትርያርክ በተዘጋጀው የሰንበት ት/ቤቶች ወጥ የሥርዓተ ትምህርት መሠረት የቅጥር የዕውቀት መደቦች እና ተከታታይ ትምህርት እንዲከናወን ያደርጋል፤
2.9.11.3. በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት በአጥቢያ፣ በሀገረ ስብከትና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ የክፍል ምዘናዎችና የዕውቅና ምስክር ወረቀቶች በየደረጃው እንዲፈጸሙ ያደርጋል፤
2.9.11.4. መንፈሳዊ የርቀት ትምህርትን ተግባራዊ ማድረግ ፤ በየአህጉረ ስብከቱ ማሻሻያ ለሚያስፈልጋቸው ማሻሻያ በመስጠት እና አዳዲስ ትምህርቶች እንዲካተቱ የርቀት ትምህርትን ዕድገት እንዲፋጠን ተገቢውን ሥራ ማከናወን፤
2.9.11.5. የሰንበት ት/ቤቱ አባላት የመንፈሳዊ ዕውቀት እና የመማር ማስተማር ሂደትን በመከታተል (በማጥናት) አዳዲስ ሥልቶችን የትግበራ ስልቶችን ለአፈጻጸም ማዘጋጀት ወደ ትምህርት እና ዕቅበት እምነት ማስተባበሪያ በየወቅቱ እንዲላክ ያደርጋል፤
2.9.11.6. ዕድሜን ፣ በሰንበት ት/ቤቱ ያለውን ቆይታ ፤ የሥራ ጠባይና ምቹ የአገልግሎት ሁኔታን መሠረት ባደረገ መንገድ የትምህርት ማዕከል ጉባኤያትን በመዘርጋት የሰንበት ት/ቤቱ አባላትን በሚወጣው ማዕቀፍ የአገልግሎት ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፤
2.9.11.7. የካትኪዝም፣ የሰንደቅ እና የተለያዩ የመማሪያ ሥራዎችን ማከናወን፤
2.9.11.8. እያንዳንዱ የሰንበት ት/ቤቱ አባል በተለያዩ መንፈሳዊ የትምህርት ሥልጠና ክህሎቱ እንዲያድግ እና ከራሱ አልፎ ለሌላው ብርሃን እንዲሆን በማድረግ እንዲሁም የመንፈሳዊ ትምህርት ድርቅ እንዳይኖር በምክክር ላይ የተመሠረተ ሥልጠና ይሰጣል፤
2.9.11.9. በሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ላይ የተተኮረ መምህራን ሥልጠና በሰፊው እንዲካሄድ በተዋቀረው መዋቅር ጋር በመናበብ ያስፈጽማል፤
2.9.11.10. ለተተኪ መምህራን የዕውቀት ማጎልበቻ ሥልጠና በየወቅቱ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
2.9.11.11. ከሰንበት ት/ቤቱ የመምህራን ዝርዝር ቋት በመነሳት በእያንዳንዱ የሰንበት ት/ቤቱ ጉባኤ ላይ መምህራንን መመደብ ፤ የተመደቡት መምህራን እና መርሐግበሩ መሪዎች በተመደቡበት ጉባኤ ላይ ማስተማራቸውን ከመርሐ ግብር እና ጉባኤያት ክፍል ጋር በመሆን መገምገም፤ እንዲሁም የትምህርታቸውን ጥልቀት፣ የዕውቀታቸውን መጠን መፈተሽ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለማሻሻያ የሚሆኑ የምክር ሐሳቦችን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል ፤
2.9.11.12. የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ አቋም የሚገልጹ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችን ያዘጋጃል፤
2.9.11.13. በሰንበት ት/ቤቱ ለሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ጽዋ ማኅበራት ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን መደበኛ መርሐ ግብር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
2.9.11.14. ከአጥቢያውና ስብከተ ወንጌል ጋር በመናበብ በአካባቢው ለሚነሱ ችግሮችና ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች የጋራ መርሐ ግብር እንዲከናወን ያደርጋል
2.9.11.15. በአጠቃላይ በሰንበት ት/ቤቶች ወጥ የሥርዓተ ትምህርት፣ በርቀት ትምህርት እና በሥልጠና አፈጻጸሞች የሚስተዋሉ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በመከታተል በተዋቀረው መዋቅር አግባብነት እንዲሻሻሉ የጥናት ምክረ ሐሳብ ያቀርባል።